top of page

ደብራችን ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ከተመሰረተ አስራ ሁለት አመታት ያስቆጠረ ሲትሆን በእነዚህ አመታት ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የአገልግሎት ዘርፉንም ሆነ የምዕመናንን ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ በማሳደግ አሁን ላለበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

ቤተክርስቲያናችን በሰሜን አሜሪካ፤ ካሊፎርኒያ ፣ ኔቫዳ እና አሪዞና ሃገረ ስብከት ውስት ይገኛል። በተለምዶ ቤይ ኤርያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፣ ከ12 ዓመታት በላይ በኪራይ ስንገለገልበት በነበረው በኦክላንድ ከተማ ውስጥ እግዚአብሔር አምላክ ፈቅዶ የራሳችን የሆነ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ልንገዛ ችለናል።

 

ከላይ እንደገለፅነው በአሁኑ ጊዜ የአገልግልት ዘርፋችንን በይበልጥ ለማሳደግም ሆነ ለማጠናከር ብሎም የተዋህዶ ልጆች በያሉበት ቦታ ሆነው የአገልግሎት ተሳታፊያችን ይሆኑ ዘንድ በማሰብ ይህንን ድረገጽ አዘጋጅተናል።

ስለሆነም በየጊዜው በድረ ገጻችን ላይ በምንለጥፋቸው መንፈሳዊ መልዕክቶች መንፈሳዊ ህይወትዎን እንዲያጎለብቱ እየጋበዝን፤ ለድረ ገጻችን ማደግ በየጊዜው ከምዕመናን የምናገኛቸው አስተያየቶች ጠቃሚ በመሆናቸው እርስዎም የበኩልዎን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ምዕመናን የሚሆኑ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችንና መረጃዎችን ስለምንለጥፍ በድጋሚ መጥተው እንዲጎበኙን እንጋብዛለን።

እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ!!

ቤተ ክርስቲያናችን
ሳምንታዊ የሰንበት መርሃ ግብር

ሥርዓተ ቅዳሴ

ከ7 AM - 9:30 AM

ትምህርተ ወንጌል

ከ 9:30 AM - 10:30 AM

አገልግሎቶች
  • ስርዓተ ተክሊል

  • ክርስትና

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። 
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። 
ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። 
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። 
በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። 
ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

​መዝ 23

ሳምንታዊ አገልግሎቶች

ሥርዓተ ቅዳሴ

ከ7 AM - 9:30 AM

ትምህርተ ወንጌል

ከ 9:30 AM - 10:30 AM

ያግኙን

አድራሻ

678 26th st.

Oakland, CA 

94612 USA

ኢሜል

dmkm510@gmail.com

መልዕክቶችን ለማግኘት ይመዝገቡ
  • Grey YouTube Icon
  • Grey Facebook Icon
bottom of page