top of page

የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት የተቋቋመው ቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት በጀመረበት ወቅት ነበር። ሰንበት ት/ቤቱ በአገልገሎቱ በዝማሬ ብቻ ሳይወሰን የቤተ ክርስቲያን ስርዓት በማስጠበቅ ረገድም ምእመናን እውነተኛውን የቤተ ክርስቲያን ድምጽ እንዲሰሙና በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል ። ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬ ለደረሰችበት ደረጃ ያበረከተው አስተዋጽኦ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ከመሆኑም ባሻገር ቤተ ክርስቲያኗ ባጋጠሟት ወቅታዊ ፈተናዎች ሁሉ ሰንበት ትምህርት ቤቱ በርትቶ በጽናት
እንዲቆምና በአገልግሎትም እንዲበረታ በአቅራቢያ ካሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በተለይ በሳን ሆዜ ፣በሳክራሜንቶ ፣ እንዲሁም ሳንፍራንሲስኮ ቤተ ክርስተያን የሰንበት ት/ቤቶች ጋር በመጣመር እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃና እየፈፀመ ላለው አገልግሎት መሳካት የጎላ ድርሻ አበርክቷል ።
የሰንበት የት/ቤቱ ከላይ የተጠቀሱትን መንፈሳዊ ተግባሮች ለመፈጸም ይረዳው ዘንድ የሚከተሉትን አሰራሮች ዘርግቷል። ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፡

1. ቤተ ክርስቲያን አምልኮቷንና አገልግሎቷን ሁሉ የምትፈጽመው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን”
እንዳለ ፤ የመተዳደሪያ ደንብ አዘጋጅቶ አባላት እንዲያውቁት አድርጎና በሰባካ ጉባዔው አጸድቆ በአገልግሎት ላይ እንዲውል አድርጓል ።
2. የሰንበት ት/ቤት ስራ አመራር በውስጡ ንዑሳን ክፍሎችን ማለትም የመዝሙርና የትምህርት ክፍል፤ የግንኙነት ክፍል፤የህጻናት ክፍል በማደራጀት አባላቱ እንደ የጸጋቸው በተለያዩ ክፍሎች ገብተው እንዲያገልግሉ በማድረግ ላይ ይገኛል።
3. ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች ጋር ግንኙነትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ሞክሯል።

 

ሰንበት ት/ቤቱ ራሱን በማጠናከር በዋናነት የሚከተሉትን መንፈሳዊ ተግባሮች አከናውኗል።


1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይለወጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ይቻል ዘንድ በት/ክፍሉ አማካኝነት ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማርና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ በሰፊው ለማሳወቅ ሃላፊነቱን መወጣት ።
2. ሕፃናትና ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን እምነትና ስርዓት ተምረው በሰንበት ት/ቤት አባል እንዲኖኑና ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት እንዲያገለለግሉ ፤ በአበው እግርም ተተክተው፣ ቤተ ክርስቲያናችን የቀደመ እምነቷንና ስርዓቷን እንደያዘች ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲችሉና በአጠቃላይ ለወገን መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ስራዎችን መስራት ።
3. የሰንበት ት/ቤት አባላት ባላቸው እውቀት ፣ ገንዘብና ጉልበት ሁለገብ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያበረክቱ ለማበረታታት ሰፊ ጥረት ማድረግ ።
4. የሰንበት ት/ቤቱ ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች የሃይማኖት ትምህርት እንዲያውቁና የአገልግሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ መስራት።

የመሠረተ ሕይወት ሰንበተ ትምህርት ቤት

ሳምንታዊ አገልግሎቶች

ሥርዓተ ቅዳሴ

ከ7 AM - 9:30 AM

ትምህርተ ወንጌል

ከ 9:30 AM - 10:30 AM

ያግኙን

አድራሻ

678 26th st.

Oakland, CA 

94612 USA

ኢሜል

dmkm510@gmail.com

መልዕክቶችን ለማግኘት ይመዝገቡ
  • Grey YouTube Icon
  • Grey Facebook Icon
bottom of page