top of page

የምክር አገልግሎት

counsling.jpg

“ወንድሞች ሆይ፥ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ…።” የሐዋርያት ሥራ ፲፫፦፲፭

የኆኀተ ሰማይ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለምዕመናንና ምዕመናት በአባቶች ካህናት የምክር አገልግሎት ትሰጣለች። የምክር አገልግሎቱም በሁለት የተከፈለ ሲሆን ይኸውም የንስሀና ማህበራዊ የምክር አገልግሎት ነው። የንስሀ የምክር አገልግሎት በሁለት የተከፈለ ሲሆን እነሱም በጉባዔና በግል የሚሰጡ ናቸው። የጉባዔ የምክር አገልግሎት በተከታታይ በትምህርትና በስብከት መልክ ለሁሉም በጋራ የሚሰጥ ሲሆን የግል የምክር አገልግሎት በቤተሰብ ደረጃ ወይም በተናጠል የሚሰጥ ነው። ማህበራዊ የምክር አገልግሎት በማህበራዊ ኑሮ ወይም በሥራ ላይ ከሚደርስ የሥነ ልቡና ጫናና ጭንቀት ለመረጋጋት በቤተሰብ ደረጃ ወይም በተናጠል በአባቶች የሚሰጥ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታና አድልዎ የምክር አገልግሎት ለሚሹ ምዕመናንና ምዕመናት በሙሉ አቅም በፈቀደ መጠን አገልግሎቱን ለመስጠት ተዘጋጅታ ትጠባበቃለች።

ሳምንታዊ አገልግሎቶች

ሥርዓተ ቅዳሴ

ከ7 AM - 9:30 AM

ትምህርተ ወንጌል

ከ 9:30 AM - 10:30 AM

ያግኙን

አድራሻ

678 26th st.

Oakland, CA 

94612 USA

ኢሜል

dmkm510@gmail.com

መልዕክቶችን ለማግኘት ይመዝገቡ
  • Grey YouTube Icon
  • Grey Facebook Icon
bottom of page